am_tn/luk/22/52.md

1.6 KiB

ወንበዴ እንደሚይዝ ሰው፣ ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ ወጣችሁን?

‹‹እኔ ወንበዴ እንደሆንሁ በማሰብ ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ ወጣችሁን? ‹‹ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው የአይሁድ መሪዎችን ለመገሠጽ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ወንበዴ እንዳይደለሁ ታውቃላችሁ፤ ግን ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ መጣችሁብኝ››

በየዕለቱ ከእናንተ ጋር ነበርሁ

‹‹በየቀኑ በመካከላችሁ ነበርሁ››

ቤተ መቅደስ ውስጥ

ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገቡ ካህናት ብቻ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቤተ መቅደስ አደባባይ›› ወይም፣ ‹‹በቤተ መቅደስ››

እጃችሁን እኔ ላይ ጫናችሁ

በዚህ ቁጥር እጆችን መጫን ሰውየውን ማሰር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ልታሰሩኝ››

የእናንተ ሰዓት

‹‹የእናንተ ጊዜ›› ወይም፣ ‹‹የምትሠሩበት ጊዜ››

የጨለማ ሥልጣን

ዐረፍተ ነገሩን ሁለት ጊዜ መድገም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጨለማ ሥልጣን ጊዜ››

የጨለማ ሥልጣን

ይህ የሚናገረው ስለ ሰይጣን አገዛዝ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጨለማ ግዛት ጊዜ›› ወይም፣ ‹‹ሰይጣን የሚሠራበት ጊዜ››