am_tn/luk/22/35.md

2.0 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ኢየሱስ ትኩረቱን ለሁሉም ደቀ መዛሙርት ወደ መናገር መልሷል፡፡

ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ በላክኋችሁ ጊዜ… የጐደለባችሁ ነበርን? እነርሱም፣ ‹‹ምንም አልጐደለብንም›› አሉ፡፡

ኢየሱስ ጥያቄውን ያነሣው በጒዞ ላይ በነበሩ ጊዜ ሕዝቡ የሚያስፈልጋቸውን ይሰጧቸው እንደ ነበር እንዲያስታወሱ ሐዋርያቱን ለመርዳት ነበር፡፡ ኢየሱስ ይህን የጠየቀው መረጃ በመጠበቅ ባይሆንም፣ ደቀ መዛሙርቱ ምንም እንዳልጐደለባቸው የሚያደርጋቸው ዐረፍተ ነገር ብቻ እስካልሆነ ድረስ በጥያቄ መልኩ ተርጒመው፡፡

እኔ በላክኋችሁ ጊዜ

ኢየሱስ ለሐዋርያቱ እየተናገረ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ‹‹እናንተ›› ለሚለው የተለየ አገላለጽ ያላቸው ቋንቋዎች በብዙ ቁጥር መጠቀም አለባቸው፡፡

ኰሮጆ

ኰሮጆ ገንዘብ መያዣ ቦርሳ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጥቅም የዋለው፣ ‹‹ገንዘብን›› ለማመልከት ነው፡፡

መያዣ ቦርሳ

‹‹የተጓዥ ቦርሳ›› ወይም፣ ‹‹የምግብ መያዣ››

ምንም

ለአንዳንድ ሰሚዎች ለውይይቱ ተጨማሪ ገለጻ መስጠት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምንም አልጐደለብንም›› ወይም፣ ‹‹የሚያስፈልገን ሁሉ ነበረን››

ሰይፍ የሌለው መጐናጸፊያውን ይሽጥ

ኢየሱስ ሰይፍ ስለሌለው አንድ ሰው እየተናገረ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰይፍ የሌለው ማንኛውም መጐናጸፊያውን መሸጥ አለበት››

መጐናጸፊያ

‹‹ኮት›› ወይም፣ ‹‹ከላይ የሚለበስ››