am_tn/luk/22/31.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢየሱስ በቀጥታ ለስምዖን እየተናገረ ነው፡፡

ስምዖን፣ ስምዖን

ኢየሱስ ስሙን ሁለቴ የጠራው ሊነግረው የፈለገው ነገር በጣም አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡

ሊያበጥራችሁ ፈለገ

‹‹እናንተ›› ሐዋርያቱን ሁሉ ይመለከታል፡፡ ‹‹እናንተ›› ለሚለው የተለየ አጠራር ያላቸው ቋንቋዎች ብዙ ቁጥርን መጠቀም አለባቸው፡፡

እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ

ይህ ማለት አንዳች ጥፋት ለማግኘት ሰይጣን ደቀ መዛሙትን መፈተን ፈለገ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስንዴ በወንፊት እንደሚያበጠር ሰው ሊያበጥራችሁ››

እኔ ግን ለአንተ ጸለይሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹አንተ›› በተለይ ስምዖንን ነው፡፡ ‹‹አንተ›› ለሚለው የተለየ አጠራር ያላቸው ቋንቋዎች ነጠላ ቁጥርን መጠቀም አለባቸው፡፡

እምነትህ እንዳይወድቅ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእምነት እንድትዘልቅ›› ወይም፣ ‹‹በእኔ በማመን እንድትዘልቅ››

ወደ ኋላ ከተመለስህ በኋላ

እዚህ ላይ ‹‹ወደ ኋላ መመለስ›› እንደ ገና ማመንን የሚያመለክት ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ገና በእኔ ማመን ስትጀምር›› ወይም፣ ‹‹እንደ ገና እኔን ማገልገል ስትጀምር››

ወንድሞችህን አበርታ

ይህ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርትን ይመለከታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አማኝ ወገኖችህን›› ወይም፣ ‹‹ሌሎች ደቀ መዛሙትን››