am_tn/luk/22/28.md

1.3 KiB

በመከራዬ ከእኔ ጋር ቆማችኋል

‹‹በመከራዬ ከእኔ ጋር ቆይታችኋል››

እኔ መንግሥት እሰጣችኋለሁ፤ አባቴ ለእኔ መንግሥት እንደ ሰጠኝ

አንዳንድ ቋንቋዎች የቅደም ተከተል ለውጥ ያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቴ ለእኔ መንግሥት እንደ ሰጠኝ እኔም መንግሥት እሰጣችኋለሁ››

መንግሥት እሰጣችኋለሁ

‹‹በእግዚአብሔር መንግሥት መሪዎች አደርጋችኋለሁ›› ወይም፣ ‹‹በመንግሥቱ ውስጥ እንድትገዙ ሥልጣን እሰጣችኋለሁ›› ወይም፣ ‹‹ነገሥታት አደርጋችኋለሁ››

አባቴ ለእኔ መንግሥት እንደ ሰጠኝ

‹‹የእርሱ መንግሥት ውስጥ እንድገዛ አባቴ ለእኔ ሥልጣን እንደ ሰጠኝ››

ዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ

ንጉሦች ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ዙፋን ላይ መቀመጥ የመግዛት ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ነገሥታት ትሠራላችሁ›› ወይም፣ ‹‹የነገሥታትን ሥራ ትሠራላችሁ››