am_tn/luk/22/26.md

2.2 KiB
Raw Permalink Blame History

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ኢየሱስ ሐዋርያትን ማስተማር ቀጥሏል

በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይሁን

‹‹እንዲህ ማድረግ የለባችሁም››

ታናሹ

በዚያ ባሕል ትልልቅ ሰዎች ይከበሩ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ መሪዎቹ ትልልቅ ሰዎች ስለ ነበሩ፣ ‹‹ሽማግሌዎች›› ይባሉ ነበር፡፡ ታናሹ ሰው መሪ የመሆን ዕድሉ ዝቅ ያለ ነው፤ አስፈላጊነቱም ዝቅ ያለ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዝቅ ያለ አስፈላጊ››

የሚያገለግል

‹‹አገልጋይ››

ነውና

ይህ ቁጥር 26 ላይ ኢየሱስ የሰጠውን ትእዛዝ ከቁጥር 27 ሙሉ ጋር ያያይዛል፡፡ ኢየሱስ አገልጋይ በመሆኑ በጣም ትልቅ የተባለው ማገልገል አለበት ማለት ነው፡፡

ታላቅ የሆነው የትኛው ነው፤… ያገልግል?

‹‹ታላቅ የተባለው የትኛው ነው… ያገልግል›› ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያነሣው በእውነት ታላቅ የሆነው የትኛው እንደሆነ ለሐዋርያት ለመግለጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታላቁ ማን እንደሆነ እንድታስቡ እፈልጋለሁ… ያገልግል››

በማእድ የተቀመጠው

‹‹የሚመገበው››

በማእድ የተቀመጠው አይደለምን?

ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር ኢየሱስ ሌላ ጥያቄ አነሣ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርግጥ ነው፤ በማእድ የተቀመጠው ከአገልጋዩ ይበልጣል!

ያም ሆኖ በመካከላችሁ እኔ እንደ አገልጋይ ነኝ

‹‹እኔ ከእናንተ ጋር ያለሁት አገልጋይ ለመሆን ነው›› ወይም፣ ‹‹እኔ ከእናንተ ጋር ያለሁ አገልጋይ እንዴት መሆን እንዳለበት ላሳያችሁ ነው›› እዚህ ላይ፣ ‹‹ያም ሆኖ›› የሚለው ቃል ሰዎች ኢየሱስ ነው ብለው በሚያስቡትና እርሱ በእርግጥ በሆነው መካከል ንጽጽር ስላለ ነው፡፡