am_tn/luk/22/17.md

1.3 KiB

የትርጒም ማስታወሻዎች ጽዋውን አነሣ

‹‹ወይን ጠጅ የነበረበትን ጽዋ አነሣ››

ምስጋና ከሰጠ በኋላ

‹‹ለእግዚአብሔር ምስጋና ከሰጠ በኋላ››

እንዲህ አለ

‹‹ለሐዋርያት እንዲህ አለ››

እርስ በርሳችሁ ተከፋፈሉት

ጽዋውን ሳይሆን ጽዋው ውስጥ የነበረውን ነው መከፋፈል ያለባቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርስ በርሳችሁ ጽዋው ውስጥ ያለውን ወይን ጠጅ ተከፋፈሉ›› ወይም፣ ‹‹እያንዳንዳችሁ ጽዋ ውስጥ ካለው የወይን ጠጅ ጠጡ፡፡››

እላችኋለሁና

ይህን ሐረግ የተጠቀመው ቀጥሎ ኢየሱስ ለሚናገረው አስፈላጊ ነገር አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

የወይን ፍሬ

ይህ የሚያመለክተው የወይኑ ፍሬ ተጨምቆ የሚወጣውን ጭማቂ ነው፡፡ ወይን ጠጅ የሚሠራው ከተብላላው የወይን ፍሬ ጭማቂ ነው፡፡

የእግዚአብሔር መንግሥት እስከምትመጣ

‹‹እግዚአብሔር መንግሥቱን እስኪመሠርት›› ወይም፣ ‹‹እግዚአብሔር መንግሥቱ ውስጥ እስኪገዛ››