am_tn/luk/22/01.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ተስማማ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ስለዚህ ሁኔታ ዳራ የሚሆን መረጃ ይሰጣሉ፡፡

አሁን

ቃሉ እዚህ ጥቅም ላይ የዋለው አዲስ ሁኔታን ለማስተዋወቅ ነው፡፡

የቂጣ በዓል

ይህ በዓል በዚህ ስም የተጠራው በዚህ ጊዜ አይሁድ እርሾ የገባበት እንጀራ ስለማይበሉ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያልቦካ እንጀራ የሚበሉበት በዓል››

ተቃርቦ ነበር

‹‹ለመጀመር ዝግጁ ነበር››

ኢየሱስን እንዴት እንደሚያስገድሉት

ካህናትና ጸሐፍት ኢየሱስን ለመግደል ሥልጣን አልነበራቸውም፣ ሌሎች እንዲገድሉት ግን ተስፋ አድርገዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢየሱስን እንዴት እንደሚያስገድሉት›› ወይም፣ ‹‹ሌሎች ኢየሱስን እንዲገድሉ ለማድረግ››

ሕዝቡን ስለ ፈሩ

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ሕዝቡ የሚያደርገው ስላስደነገጣቸው›› ወይም 2) ‹‹ሕዝቡ ኢየሱስን ንጉሥ ያደርጉታል ብለው ስለ ፈሩ››