am_tn/luk/21/37.md

1.5 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ይህ ሉቃስ 20፥1 ላይ የጀመረው ታሪክ ክፍል የመጨረሻ ነው፡፡ እነዚህ ቁጥሮች የዋናው ታሪክ ክፍል እስኪያበቃ ድረስ ቀጣይ ስለሆነው ድርጊት ይናገራሉ፡፡

እርሱ እያስተማረ በነበረበት ቀኖች

‹‹እያስተማረ በነበረ ቀን›› ወይም፣ ‹‹በየቀኑ ሲያስተምር›› ቀጥሎ ያሉት ቁጥሮች እርሱ ከመሞቱ በፊት በነበረው ሳምንት ኢየሱስና ሕዝቡ ስላደረጓቸው ነገሮች ይናገራሉ፡፡

ቤተ መቅደስ ውስጥ

ቤተ መቅደስ ውስጥ መግባት የሚፈቀድላቸው ካህናት ብቻ ነበሩ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቤተ መቅደስ›› ወይም፣ ‹‹ቤተ መቅደሱ ግቢ ውስጥ››

በሌሊት እርሱ ሄዶ

‹‹በሌሊት እርሱ ከከተማ ውጪ ሄዶ›› ወይም፣ ‹‹በየሌሊቱ ይሄድ ነበር››

ሕዝቡ ሁሉ

‹‹ሁሉ›› የሚለው የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ እንደ ነበር አጽንዖት ለመስጠት ግነት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ብዛት ያለው ሕዝብ ከተማው ውስጥ›› ወይም፣ ‹‹ከተማው ውስጥ ያለው ሁሉም ሰው››

ማልደው ይመጡ ነበር

‹‹በየጠዋቱ ይመጡ ነበር››

እርሱን ለመስማት

‹‹ሲያስተምር ለመስማት››