am_tn/luk/21/34.md

1.9 KiB

ልባችሁ እንዳይከብድ

‹‹ልብ›› የሰውን አእምሮና ሐሳብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዳትያዙ››

እንዳይከብድ

ኀጢአት ሰው የሚሸከመው ሸክም እንደሆነ እዚህ ላይ ኢየሱስ ይናገራል፡፡

ከመጠጥ የተነሣ

‹‹ብዙ ወይን ጠጅ መጠጣት እናንተ ላይ የሚያመጣው›› ወይም፣ ‹‹ስካር››

የሕይወት ጭንቀት

‹‹ስለዚህ ሕይወት በብዛት መጨነቅ››

ቀኑ እንደ ወጥመድ በድንገት እንዳይዛችሁ

እንስሳው ሳይጠብቀው ወጥመድ በድንገት እንደሚዘጋበት፣ ያም ቀን ሰዎች ባልጠበቁት ቀን ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወጥመድ እንስሳው ላይ በድንገት እንደሚዘጋ፣ ያም ቀን ባልጠበቃችሁት ጊዜ ይሆናል››

ያ ቀን በድንገት ይዘጋባችኃል

ላልተዘጋጁና ላልጠበቁ ሰዎች የዚያ ቀን መምጣት በድንገት ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕይወት፤ ካልተጠነቀቃችሁ ያ ቀን በድንገት ይዘጋባችኃል››

ያ ቀን

ይህ የሚያመለክተው መሲሑ የሚመለስበትን ቀን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰው ልጅ የሚመጣበት ቀን››

በሁሉም ላይ ይመጣል

‹‹ሁሉንም ይመለከታል›› ወይም፣ ‹‹በዚያ ቀን የሚሆነው ሁሉም ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡››

በመላው ምድር ፊት

የላይኛው የምድር ክፍል እንደ የሰው ፊት ተነግሯል፡፡ ይህ ውጫዊ ክፍል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድር ሁሉ ገጽታ ላይ›› ወይም፣ ‹‹በመላው ምድር ላይ››