am_tn/luk/21/29.md

1.1 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ማስተማሩን ሲቀጥል ምሳሌ እየነገራቸው ነው፡፡

ሲያቆጠቁጡ

‹‹አዲስ ቅጠል ማደግ ሲጀምር››

በጋ ቀርቦአል

‹‹በጋ ሊጀምር ነው›› በእስራኤል በጋ የሚመጣው የበለስ ዛፍ ቅጠሎችን ማቆጥቆጥ ተከትሎ ሲሆን፣ በለስ የሚያፈራበት ጊዜ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የመከር ጊዜ ሊጀምር ነው››

እናንተም እነዚህ ነገሮች ሲሆኑ ስታዩ

የበለስ ቅጠሎች ማቆጥቆጥ በጋ መምጣቱን እንደሚያመለክቱ፣ ኢየሱስ የተናገራቸው ምልክቶች መታየትም የእግዚአብሔር መንግሥት መምጣቱን ያመለክታሉ፡፡

የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች

‹‹እግዚአብሔር በቅርቡ መንግሥቱን ይመሠርታል›› አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር በቅርቡ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል››