am_tn/luk/21/27.md

1.7 KiB

የሰው ልጅ ሲመጣ

ኢየሱስ ስለ ራሱ እየተናገረ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ፣ የሰው ልጅ ስመጣ››

በደመና ሲመጣ

‹‹በደመና ውስጥ ሲመጣ››

በኀይልና በታላቅ ክብር

እዚህ ላይ፣ ‹‹ኀይል›› ዓለም ላይ ለመፍረድ የእርሱን ሥልጣን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ ‹‹ክብር›› ደማቅ ብርሃንን ሊያመለክት ይችላል፡፡ አንዳንዴ እግዚአብሔር በደማቅ ብርሃን ታላቅነቱን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀያልና ክቡር›› ወይም፣ እርሱ ኀያልና እጅግ ክቡር ይሆናል››

ቁሙ

ሰዎች ሲፈሩ እንዳይታዩ ወይም ጉዳት እንዳይደርስባቸው በጣም ዝቅ ይላሉ፡፡ የሚያስፈራቸው ነገር ሳይኖር ግን ይነሣሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በልበ ሙሉነት ቁሙ››

ራሳችሁን ቀና አድርጉ

ራስን ቀና ማድረግ ወደ ላይ ማየት ማለት ነው፡፡ ራሳቸውን ወደ ላይ ቀና ሲያደርጉ አዳኛቸው ወደ እነርሱ ሲመጣ ያያሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተመልከቱ››

መዳናችሁ ስለ ቀረበ

የሚያድን እግዚአብሔር አንዳንዴ እርሱ የሚያደርገው መዳን እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ‹‹መዳን›› የሚለው ቃል የነገር ስም ስለሆነ እንደ ግሥ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ቶሎ ስለሚያድናችሁ››