am_tn/luk/21/23.md

2.4 KiB

ለሚያጠቡ

‹‹ልጆቻቸውን ለሚያጠቡ እናቶች››

በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ ይሆናል

ይህም ማለት፣ 1) በምድሪቱ የሚኖሩ መከራ ይደርስባቸዋል፤ ወይም 2) ምድሪቱ ላይ መከራ ይደርስባታል፡፡

ሕዝብ ላይ ቁጣ

‹‹ሕዝቡ ላይ ቁጣ የሚሆንበት ጊዜ›› እግዚአብሔር ይህን ቁጣ ያመጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ ሕዝብ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣል›› ወይም፣ ‹‹እግዚአብሔር በጣም ይቆጣል ይህንም ሕዝብ ይቀጣል››

በሰይፍ ስለት ይወድቃሉ

‹‹በሰይፍ ስለት ይገደላሉ›› እዚህ ላይ፣ ‹‹በሰይፍ ስለት ይገደላሉ›› የሚለው በጠላት ወታደሮች መገደልን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጠላት ወታደሮች ይገድሏቸዋል››

ወደ አሕዛብም ሁሉ በምርኮ ይወስዳሉ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቻቸው ይይዟቸዋል፤ ወደ ሌሎች አገሮችም ይወስዷቸዋል››

ወደ አሕዛብ ሁሉ

‹‹ሁሉ›› የሚለው ወደ ብዙ አገሮች እንደሚወሰዱ አጽንዖት ለመስጠት ጥቅም ላይ የዋለ ግነት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ሌሎች ብዙ አገሮች››

ኢየሩሳሌም በአሕዛብ ትረገጣለች

ይህም ማለት፣ 1) አሕዛብ ኢየሩሳሌምን ድል አድርገው ይይዟታል፡፡ ወይም 2) አሕዛብ የኢየሩሳሌም ከተማን ይጠፋሉ ወይም 3) አሕዛብ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ይደመስሳሉ፡፡

በአሕዛብ ትረገጣለች

ተለዋጭ ዘይቤው ኢየሩሳሌም የሌላ አገር ሰዎች እንደሚራመዱባትና በእግራቸውም እንደሚያደቋት ይናገራል፡፡ ይህ ባርነትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በአሕዛብ ድል ትሆናለች›› ወይም፣ ‹‹በሌላ ሕዝብ ትደመሰሳለች››

የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአሕዛብ ወቅት እስኪያበቃ››