am_tn/luk/21/14.md

1.2 KiB

ስለዚህ

‹‹በዚህ ምክንያት›› ከሉቃስ 21፥10 ጀምሮ ኢየሱስ የተናገረውን ማንኛውንም ነገር ይመለከታል፡፡

በልባችሁ አትወስኑ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ልብ›› የሰዎቹን አእምሮ ይወክላል፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አእምሮአችሁን እንዳታዘጋጁ›› ወይም፣ ‹‹በቁርጥ እንዳትወስኑ››

ከጊዜው በፊት መከላከያ አታብጁ

‹‹ለሚነሣባችሁ ክስ ራሳችሁን ለመከላከል ምን እንደምትሉ ከጊዜው በፊት አታስቡ››

ተቃዋሚዎቻችሁ ሁሉ ሊቋቋሙትና ሊያስተባብሉት የማይችሉት ጥበብ

‹‹ከተቃዋሚዎቻችሁ አንዱ እንኳ፣ መቋቋምና ማስተባበል የማይችለው ጥበብ››

ቃላትና ጥበብ እሰጣችኃለሁ

‹‹የምትናገሩትን ጥበብ እሰጣችኃለሁ››

ቃላትና ጥበብ

ይህን በአንድ ዐረፍተ ነገር ማጣመር ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጥበብ ቃል›› ወይም፣ ‹‹ጠቢብ ቃሎች››