am_tn/luk/21/10.md

1.8 KiB

ከዚያም እንዲህ አላቸው

‹‹ከዚያም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ›› ይህ ካለፈው ቁጥር የቀጠለ የኢየሱስ ንግግር በመሆኑ፣ አንዳንድ ቋንቋዎች፣ ‹‹ከዚያም እንዲህ አላቸው›› የሚለውን አይጠቀሙም፡፡

ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሣል

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሕዝብ›› የሕዝብ ሰዎችን፣ ‹‹ይነሣል›› የሚለው ደግሞ፣ ‹‹ያጠቃል›› የሚለውን የሚወክል ሊሆን ይችላል፡፡ ‹‹ሕዝብ›› የሚለው ቃል አጠቃላይ ሕዝቦችን እንጂ፣ አንድን ሕዝብ ማለት አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንድ ሕዝብ የሌላውን ሕዝብ ያጠቃል›› ወይም፣ ‹‹የአንዳንድ ሕዝቦች ሌሎችን ሕዝቦች ያጠቃሉ››

ሕዝብ

ይህ አገሮችን ሳይሆን የተለያዩ ብሔሮችን ይወክላል፡፡

መንግሥት በመንግሥት ላይ

‹‹ይነሣል›› የሚለው ቃል ካለፈው ሐረግ ውስጠ ታዋቂ ሲሆን፣ ያጠቃል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል›› ወይም፣ ‹‹የአንዳንድ መንግሥታት ሕዝብ የሌላውን መንግሥታት ሕዝብ ይጠቃሉ››

በተለያዩ ቦታዎች ራብና ቸነፈር

‹‹ይኖራል›› የሚለው ቃል ካለፈው ሐረግ ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በብዙ ቦታዎች ራብና ቸነፈር ይሆናል›› ወይም፣ ‹‹በተለያዩ ቦታዎች የራብና የበሽታ ጊዜ ይሆናል››