am_tn/luk/21/07.md

2.1 KiB

እርሱን ጠየቁት

‹‹ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን ጠየቁት›› ወይም፣ ‹‹የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጠየቁት››

እነዚህ ነገሮች

ይህ ጠላቶች ቤተ መቅደሱን እንደሚያፈርሱ ኢየሱስ የተናገረውን ያመለክታል፡፡

እንዳትሳሳቱ

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እየተናገረ ነበር፡፡ ‹‹እናንተ›› ብዙ ቁጥር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሐሰት እንዳታምኑ›› ወይም፣ ‹‹ማንም እንዳያሳስታችሁ››

በስሜ

እርሱን እንወክላለን የሚሉ ሰዎች በእርሱ ስም ይመጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ነኝ እያሉ›› ወይም፣ ‹‹የእኔ ሥልጣን እንዳለው እየተናገረ››

እኔ እርሱ ነኝ

‹‹እኔ ክርስቶስ ነኝ›› ወይም፣ ‹‹እኔ መሲሑ ነኝ››

አትከተሏቸው

‹‹አትመኗቸው›› ወይም፣ ‹‹ደቀ መዛሙርቶቻቸው አትሁኑ››

ጦርነትና ዐመፅ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ጦርነት›› በአገሮች መካከል የሚደረግ ውጊያን፣ ‹‹ዐመፅ›› ሰዎች ከመሪዎቻቸው ጋር ወይም በአገራቸው ካሉት ሌሎች ጋር የሚያደርጉትን ግጭት ሊያመለክት ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጦርነትና ረብሻ›› ወይም፣ ‹‹ጦርነትና አብዮት››

አትሸበሩ

‹‹እነዚህ ነገሮች አያሸብሯችሁ›› ወይም፣ ‹‹አትፍሩ››

መጨረሻው ወዲያው አይመጣም

ይህ የመጨረሻውን ፍርድ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከጦርነቱና ከዐመፁ በኃላ ወዲያውኑ የዓለም ፍጻሜ አይሆንም›› ወይም፣ ‹‹እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኃላ ወዲያው ዓለም አይጠፋም››

መጨረሻው

‹‹የማንኛውም ነገር መጨረሻ›› ወይም፣ ‹‹የዘመን መጨረሻ››