am_tn/luk/20/45.md

1.5 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

አሁን ኢየሱስ ትኩረቱን በቀጥታ ደቀመዛሙርቱ ላይ አድርጐ በዋናነት ስለ እነርሱ መናገር ጀመረ

ተጠንቀቁ

‹‹ተጠበቁ››

ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሰው መዞር ከሚወዱ

ረጅም ቀሚስ ምን ያህል አስፈላጊ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አስፈላጊ ቀሚሳቸውን ለብሰው መዞር የሚወዱ››

የመበለቶችን ቤት የሚውጡ

‹‹የመበለቶችንም ቤት ይበላሉ›› ጸሐፍት የመበለቶችን ቤት የሚበሉ የተራቡ እንስሳት እንደ ሆኑ ተነግሯል፡፡ ‹‹ቤት›› የመበለቶቹን መኖሪያና ንብረታቸውን ሁሉ የሚያደርጉበትን ቦታ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከመበለቶቹም ንብረታቸውን ሁሉ ይወስዳሉ››

ለታይታ ብለውም ረጅም ጸሎት ያደርጋሉ

‹‹ዳድቅ እንደሆኑ ለማሳየት ረጅም ጸሎት ያደርጋሉ›› ወይም፣ ‹‹ሰዎች እንዲያዩዋቸው ረጅም ጸሎት ያደርጋሉ››

እንዲህ ያሉ ሰዎች የበለጠውን ፍርድ ይቀበላሉ

‹‹የበለጠ ከባድ ፍርድ ይቀበላሉ›› ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር በእርግጥ በጽኑ ይቀጣቸዋል››