am_tn/luk/20/19.md

1.4 KiB

እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ

በዚህ ቁጥር፣ ሰው ላይ ‹‹እጅ መጫን›› ሰውየውን ማሰር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኢየሱስን የሚያስሩበት መንገድ ፈለጉ››

በዚያ ሰዓት

‹‹ወዲያው››

ሕዝቡን ፈሩ

ወዲያውኑ ኢየሱስን ያላሰሩት በዚህ ምክንያት ነበር፡፡ ሕዝቡ ኢየሱስን ያከብሩት ነበር፤ እርሱን ካሰሩት ሕዝቡ እነርሱ ላይ የሚያደርገውን የሃይማኖት መሪዎቹ ፈሩ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝቡን ስለ ፈሩ አላሰሩትም››

ሰላዮች ላኩ

‹‹ጸሐፍትና የካህናት አለቆች ኢየሱስን የሚከታተሉ ሰላዮች ላኩ››

በንግግሩ ስሕተት ሊያገኙበት

‹‹አንዳች መጥፎ ነገር ሲናገር ኢየሱስን መክሰስ ስለ ፈለጉ››

ለገዥው ኀይልና ሥልጣን

‹‹ግዛት›› እና ‹‹ሥልጣን›› አገረ ገዥው ኢየሱስ ላይ እንዲፈርድ እንደሚፈልጉ ለማመልከት ሁለት መንገዶች ናቸው፡፡ በአንዱ ወይም በሁለቱ አገላለጾች ሊተረጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ገዢው ኢየሱስን እንዲቀጣ››