am_tn/luk/20/17.md

2.2 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ኢየሱስ ሕዝቡን ማስተማር ቀጥሏል፡፡

ኢየሱስ ግን ተመለከታቸው

‹‹ኢየሱስ ግን ትኩር ብሎ አያቸው›› ወይም፣ ‹‹እርሱ ግን በቀጥታ አያቸው›› ይህን ያደረገው የነገራቸውን በመረዳታቸው ተጠያቂዎች መሆናቸውን ለማስገንዘብ ነው፡፡

‹ድንጋይ… ግንበኞች› ተብሎ የተጻፈው ቃል ትርጒም ምንድነው?

ኢየሱስ ጥያቄውን ያቀረበው ሕዝቡን ለማስተማር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ድንጋይ… ግንበኞች›› ተብሎ የተጻፈውን መረዳት ይኖርባችኃል፡፡››

የተጻፈው

‹‹ይህ ቃል››

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ

ይህ ከመዝሙር መጽሐፍ ትንቢቶች ሦስት ተለዋጭ ዘይቤዎች የመጀመሪያው ነው፡፡ ይህኛው መሲሑ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እግዚአብሔር ግን በጣም ጠቃሚ ያደረገው ድንጋይ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ግንበኞች

ይህ የሚያመለክተው መሲሑ ኢየሱስን የናቁትን የሃይማኖት መሪዎች ነው፡፡

የማእዘን ድንጋይ

‹‹የሕንፃው ዋና ድንጋይ›› ወይም፣ ‹‹ከሕንፃው በጣም ጠቃሚ የሆነው ድንጋይ››

በእርሱ ላይ የሚወድቅ ሁሉ… ይደቃል

ይህ ሁለተኛው ተለዋጭ ዘይቤ መሲሑን የናቁ ሰዎች ድንጋይ ላይ ወድቀው እንደሚጐዱ ሰዎች መሆናቸውን ይናገራል፡፡

ይደቃል

ይህ ድንጋይ ላይ የመውደቅ ውጤት ነው፡፡ በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እስኪደቅ ይሰባበራል››

በላዩ የሚወድቅበት ግን

‹‹ድንጋዩ የሚወድቅበት ግን›› ይህ ሦስተኛው ተለዋጭ ዘይቤ እነርሱ ላይ ወድቆ እንደሚፈጭ ግዙፍ ድንጋይ መሲሑ የናቁት ላይ እንደሚፈርድ ያመለክታል፡፡