am_tn/luk/20/09.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ለሰዎች ምሳሌ መናገር ጀመረ፡፡

ለገበሬች አከራዬ

‹‹በከፈሉት መጠን የወይን ገበሬዎች እንዲጠቀሙበት ፈቀደ›› ወይም፣ ‹‹ገበሬዎቹ እንዲጠቀሙበትና በኃላ እንዲከፍሉት ፈቀደ›› ክፍያው በገንዘብ ወይም በምርቱ መጠን ሊሆን ይችላል፡፡

የወይን ገበሬዎች

እነዚህ የወይን ፍሬ የሚያመርቱ ሰዎች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወይን የሚያለሙ ገበሬዎች››

በተወሰነው ጊዜ

‹‹ሊከፍሉት የተስማሙበት ጊዜ›› ይህ ምርቱ ሲደርስ ሊሆን ይችላል፡፡

ከወይኑ እርሻ ፍሬ

‹‹ከፍሬው ጥቂቱን›› ወይም፣ ‹‹ከእርሻው ካመረቱት ጥቂቱን›› ይህም ከፍሬው የሠሩት ነገር ፍሬውን ሸጠው ያገኙት ገንዘብ ሊሆን ይችላል፡፡

ባዶ እጁን ሰደዱት

ባዶ እጅ፣ ‹‹ምንም› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምንም ሳይከፍሉ ሰደዱት›› ወይም፣ ‹‹ፍሬ ሳይሰጡ ሰደዱት››