am_tn/luk/20/03.md

1.4 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ኢየሱስ ለካህናት አለቆች፣ ለጸሐፍትና ለሽማግሌዎች መልስ ሰጠ፡፡

እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው

‹‹ኢየሱስ መለሰ››

እኔ እጠይቃችኃለሁ፤ እናንተም ንገሩኝ

‹‹እኔ እጠይቃችኃለሁ›› የሚለው ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ ‹‹እናንተም ንገሩኝ›› ትእዛዝ ነው፡፡

ከሰማይ ነው ወይስ ከሰው

የዮሐንስ ሥልጣን ከሰማይ መሆኑን ኢየሱስ ያውቃል፤ ስለዚህም የጠየቀው መረጃ እንዲሰጡት አይደለም፡፡ የጠየቀው የአይሁድ መሪዎች የሚያስቡትን ሰሚዎቹ ፊት እንዲናገሩ ነው፡፡ ጥያቄው መልስ የማያሻው ቢሆንም፣ እንደ ጥያቄ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዮሐንስ ሰዎችን የማጥመቅ ሥልጣን ከሰማይ የመጣ ይመስላችኃል ወይስ ከሰው? ወይም፣ ‹‹ዮሐንስ ሰዎችን እንዲያጠምቅ የነገረው እግዚአብሔር ነው ወይስ ሰው?

ከሰማይ

‹‹ከእግዚአብሔር›› አይሁድ እግዚአብሔርን፣ ‹‹ያህዌ›› በሚለው ስሙ መጥራት አይፈልጉም፡፡ ስለ እርሱ ሲናገሩ ብዙውን ጊዜ፣ ‹‹ሰማይ›› በሚለው ቃል ይጠቀማሉ፡፡