am_tn/luk/19/43.md

2.7 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ መናገሩን ቀጥሏል

እናም

ቀጥሎ የሚሆነው ለኢየሱስ ሀዘን ምክንያት ነው

ጠላቶችሽ በአንቺ ላይ …ቀን ይመጣልና

ይህ የሚያመለክተው አስጨናቂ ወቅት እንደሚያጋጥማቸው ነው፡፡ አንዳድ ቋንቋዎች "ስለሚመጣው" ጊዜ አይናገሩም፡፡ "እነዚህ ነገሮች ወደፊት በአንቺ ላይ ይደርሳሉ፡ ጠላቶችሽ…" ወይም "በቶሎ አስጨናቂ ጊዜ ይገጥምሻል፡፡ ጠላቶችሽ…"

አንቺ…የአንቺ

"አንቺ" የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ለከተማይቱ የሚናገረው እንደ ሴት አድርጓት፡፡ ነገር ግን ይህ በእናንተ ቋንቋ ተፈጥሯዊ ካልሆነ የከተማዋን ሰዎች ለማመልከት "እናንተ" የሚለውን ብዙ ቁጥር መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች እና የስርአተ ነጥብ ምልክት/ቃለአጋኖ የሚሉትን ይመልከቱ)

ቅጥር

ይህ የሚያመለክተው ሰዎች ከከተማዋ ውጭ እንዳይገቡ የሚያግድን ግንብ ነው፡፡

ወደ ምድር ይጥሉሻል ደግሞም ከአንቺ ጋር ልጆችሽን

ኢየሱስ ለከተማይቱ ሰዎች የሚናገረው ለከተማይቱ ለራሷ እንደሚናገር አድርጎ ነው፡፡ በከተማዋ ለሚኖሩ ሰዎች የሴትየዋ ልጆች እንደሆኑ እና ስለዚህም የከተማዋ ልጆች እንደሆኑ አድርጎ ነው፡፡ ከተማይቱን መምታት ቅጥሯን እና አጥሯን መደምሰስ ማለት ሲሆን፣ልጆችዋን መምታት ማትም በውስጧ የሚኖሩትን ሰዋች መግደል ማለት ነው፡፡ "ሙሉ ለሙሉ ይደመስሱሻል፣ ደግሞም በውስጥሽ የሚኖሩትን ሁሉ ይገድላሉ" ወይም "ከተማችሁን ሙሉ ለሙሉ ይደመስሳሉ፣ ደግሞም ሁላችሁንም ይገድላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የስርአተ ነጥብ ምልክት/ቃለአጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም

"አንዲትንም ድንጋይ በስፍራዋ አይተዉም፡፡" ይህ ጠላቶች በድንጋይ የተገነባችውን ከተማ ሙሉ ለሙሉ እንሚደመስሱ በኩሸት ለመግለጽ የቀረበ ነው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

አላወቅሽም

"እውቅና አልሰጠሸም"