am_tn/luk/19/37.md

1.6 KiB

አሁን እየቀረበ ሲመጣ

"ኢየሱስ እየቀረበ ሲመጣ፡፡" የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር ይጓዙ ነበር፡፡

የደብረዘይት ተራራ ቁልቁል በሚወርድበት

"መንገዱ ከደብረዘይት ተራራ ቁልቁል ሲሄድ"

እነርሱ ባዩት ታላላቅ ሥራዎች

"ኢየሱስ ሲሰራ ባዩት ታላላቅ ነገሮች"

ንጉሡ የተባረከ ነው

ይህን ይናገሩ የነበረው ስለ ኢየሱስ ነበር፡፡

በጌታ ስም

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚለው የሚያመለክተው ስለ ሀይል እና ስልጣን ነው፡፡ እንደዚሁም፣ "ጌታ" የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰማይ ሰላም

"በሰማይ ሰላም ይሁን" ወይም "በሰማይ ሰላም ማየት እንሻለን"

በላይ ክብር ይሁን

"በላይ ክብር ይሁን" ወይም "ክብር በላይ ማየት እንፈልጋለን፡፡" "በላይ" የሚለው ቃል የሚመለክተው ሰማይን ነው፤ ይህም በሰማይ ለሚኖረው ለእግዚአብሔር ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ሁሉም በሰማይ ላለው ለእግዚአብሔር ክብር ይስጥ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)