am_tn/luk/19/29.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ደረሰ፡፡

እንዲህም ሆነ

እዚህ ስፍራ ይህ ሀረግ የዋለው በታሪኩ ውስጥ አስፈላጊ ትዕይንተን ለማመልከት ነው፡፡ የእናንተ ቋንቋ ይህንን ለማድረግ መንገድ ካለው፣ እዚህ ላይ ያንን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ (አዲስ ትዕይንት ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

በተቃረበ ጊዜ

"እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስን ነው፡፡ የእርሱ ዳመዛሙርትም አብረውት ይጓዙ ነበር፡፡

ቤተ ፋጌ

ቤተ ፋጌ በደብረዘይት ተራራ የነበረች (ዛሬም ያለች) መንደር ስትሆን፣ ከቄድሮን ሸለቆ ባሻገር ትገኛለች፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ደብረዘይት የሚባል ተራራ

"ደብረዘይት የሚባል ተራራ/ኮረብታ" ወይም "‘የወይራ ፍሬ ተራራ' ተብሎ የሚጠራ ኮረብታ"

ውርንጫ

"ውርንጭላ አህያ" ወይም " ገና እያደገ የሚገኝ ለመጋለቢያ የሚውል እንስሳ"

ማንም ያልተቀመጠበት/ያልጋለበው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማንም ያልተቀመጠበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ቢጠይቃችሁ…ይፈልገዋል በሉ

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ገና ያልተጠየቀን ጥያቄ ስለመመለስ ይነግራቸዋል፡፡ ሆኖም፣ በመንደሯ የሚኖሩ ሰዎች ጥያቄውን ይጠይቃሉ፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ሰው ቢጠይቃችሁ፣ ‘ለምን ትፈቱታላችሁ'? ቢላችሁ

ውስጣዊ ጥቅሱ እንደ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ጥቅስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም ለምን ትፈቱታላችሁ ብሎ ቢጠይቃችሁ፣ እንዲህ በሉ" (በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅሶች)