am_tn/luk/19/26.md

2.1 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ በሉቃስ 19፡11 የጀመረውን ግብረገባዊ ምሳሌ መናገሩን ቀጠለ፡፡

እንዲህ እላችኋለሁ

ይህ የንጉሡ ንግግር ነበር፡፡ አንዳንድ ተርጓሚዎች ይህንን ቁጥር "ንጉሡም እንዲህ ሲል መለሰ፣ ‘እኔ ለእናንተ እላችኋለሁ'" ወይም "ነገር ግን ንጉሡ ‘ይህን እላችኋለሁ'" ብለው ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡

ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል

እርሱ ያለው ምናኑን በታማኝነት በመጠቀም ያገኘው ገንዘብ መሆኑ በውስጠ ታዋቂነት ተጠቁሟል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የተሰጠውን በሚገባ ለተጠቀመ ሁሉ፣ እኔ ተጨማሪ እሰጠዋለሁ" ወይም "እኔ የሰጠሁትን ሁሉ በሚገባ ለሚጠቀም ሁሉ እኔ ተጨማሪ እሰጠዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከሌለው ከእርሱ

ገንዘብ ሳይኖረው የቀረበት ምክንያት ምናኑን በታማኝነት አለመጠቀሙ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ "እኔ የሰጠሁትን በሚገባ ከማይጠቀምበት ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይወሰድበታል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እኔ ከእርሱ እወስድበታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ የእኔ ጠላቶች

ጠላቶች የተባሉት በቀጥታ በዚያ እስከሌሎ ድረስ፣ አንዳንድ ቋንቋዎች "እነዚያ የእኔ ጠላቶች" ሊሉ ይችላሉ፡፡