am_tn/luk/19/22.md

2.0 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ በሉቃስ 19፡11 የጀመረውን ግብረገባዊ ምሳሌ መናገሩን ቀጠለ፡፡

በአንደበትህ ቃል

የእርሱ "ቃላት" የሚለው የሚያመለክተው እርሱ የተናገረውን በሙሉ ነው፡፡ "አንተ በተናገርከው መሰረት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ እኔ አስገዳጅ/ጨካኝ ሰው እንደሆንኩ ታውቃለህ

ልዑሉ አገልጋዩ ስለ እርሱ የተናገረውን ይደግማል፡፡ ነገሩ እውነት ነው እያለ አይደለም፡፡ "አንተ እኔን ጨካኝ ሰው ነው ብለሃል"

ገንዘቤን እንዲወልድ ለምን በ…. አላስቀመጥክም?

ልዑሉ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ክፉውን አገልጋይ ለመገሰጽ ነው፡፡ "እንዲወልድ ገንዘቤን በ… ማስቀመጥ ነበረብህ፡፡" (ቃለምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ገንዘቤን በባንክ ማስቀመጥ

"ገንዘቤን ለባንክ ማበደር፡፡" ባንክ በሌላቸው ባህሎች ይህንን "ገንዘቤን ለሰው ማበደር" በሚል ሊተረጉሙ ይችላሉ፡፡

ባንክ

ባንክ የሰዎችን ገንዘብ በአስተማማኝነት የሚይዝ የንግድ ተቋም ነው፡፡ ባንክ ያንን ገንዘብ በትርፍ ለሌሎች ያበድራል፡፡ ስለዚህም በባንኩ ገንዘባቸው ላስቀመጡ፣ ተጨማሪ መጠን ወይም ወለድ፣ ይከፍላል፡፡

ከወለዱ ጋር እወስድ ነበር

"ተቀማጩን ገንዘብ ከሚያስገኘው ወለድ ጭምር እወስድ ነበር" ወይም "ከእርሱ ትርፍ አገኝበት ነበር"

ወለድ

ትርፍ ገንዘባቸውን በባንክ ላስቀመጡ ሰዎች የሚከፍለው ገንዘብ ነው፡፡