am_tn/luk/19/18.md

1.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ በሉቃስ 19፡11 የጀመረውን ግብረገባዊ ምሳሌ መናገሩን ቀጠለ፡፡

ሁለተኛው

"ሁለተኛው አገልጋይ" (ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ምናንህ፣ ጌታ ሆይ፣ ተጨማሪ አምስት ምናን አተረፈ

አገልጋዩ ያተረፈ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ "ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ተጨማሪ አምስት ምናን እንዲያተርፍ አድርጌያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ምናን

አንድ ምናን 600 ግራም ነው፤ ምናልባት የሰጣቸው ብር የተሰኘውን ማዕድን ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንድ ምናን የ100 ቀን ሥራ ደሞዝ ያክላል፤ ሰዎች ወደ አራት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ሰርተው የሚያገኙት ክፍያ ነው፡፡ ይህ በሉቃስ 19፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የክብደት መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)

በአምስት ከተሞች ላይ ሹሜሃለሁ

"በአምስት ከተሞች ላይ ስልጣን ይኖርሃል"