am_tn/luk/19/16.md

1.7 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ በሉቃስ 19፡11 የጀመረውን ግብረገባዊ ምሳሌ መናገሩን ቀጠለ፡፡

የመጀመሪያው

"የመጀመሪያው አገልጋይ" (ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቱ ቀረቡ

"ልዑሉ ፊት ቀረቡ"

ምናንህ ተጨማሪ አስር ምናን አተረፈ

አገልጋዩ ያተረፈ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ "ምናንህ ተጨማሪ አስር ምናን እንዲያተርፍ አድርጌያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ምናን

አንድ ምናን 600 ግራም ነው፤ ምናልባት የሰጣቸው ብር የተሰኘውን ማዕድን ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንድ ምናን የ100 ቀን ሥራ ደሞዝ ያክላል፤ ሰዎች ወደ አራት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ሰርተው የሚያገኙት ክፍያ ነው፡፡ ይህ በሉቃስ 19፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የክብደት መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም አደረግህ

"አንተ መልካም ሰርተሃል፡፡" ቋንቋችሁ ቀጣሪ በትክክል መሰራቱን የሚያረጋግጥበት አገላለጽ/ሀረግ ሊኖር ይችላል፡፡ "ጥሩ ሰርተሃል" እንደሚለው አይነት፡፡

በጣም ጥቂት

ይህ ልዑሉ በግልጽ ብዙ ገንዘብ ብሎ የማይቆጥረውን፣ አንድ ምናን ያመለክታል፡፡