am_tn/luk/19/13.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ በሉቃስ 19፡11 የጀመረውን ግብረገባዊ ምሳሌ መናገሩን ቀጠለ፡፡

እርሱ ጠራቸው

"ልዑሉ ጠራቸው፡፡" ሰውየው ይህንን ያደረገው የንጉሥነትን ማዕረግ/የእርሱን መንግሥት ለመቀበል ከመሄዱ አስቀድሞ እንደሆነ መግለጹ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ "ከመሄዱ አስቀድሞ ጠራቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

አስር ምናን ሰጣቸው

"ለእያንዳንዳቸው አንድ ምናን ሰጣቸው"

አስር ምናን

አንድ ምናን 600 ግራም ነው፤ ምናላባት ሰጣቸው ብር የተሰኘውን ማዕድን ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንድ ምናን የ100 ቀን ሥራ ደሞዝ ያክላል፤ ሰዎች ወደ አራት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ሰርተው የሚያገኙት ክፍያ ነው፡፡ ስለዚህ አስር ምናን አንድ የቀን ሥራተኛ በሶስተ አመታት የሚከፈለው የክፍያ መጠን ነው፡፡ "አስር ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸው ሳንቲሞች" ወይም "እጅግ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ቁጥሮች እና ክብደት መለኪያ የሚሉትን ይመልከቱ)

ንግድ ማካሄድ

"በዚህ ገንዘብ መነገድ" ወይም "ይህንን ገንዘብ ተጨማሪ ለማግኘት መጠቀም"

የእርሱ ዜጎች

"የእርሱ አገር ሰዎች"

መልዕክተኛ

"እነርሱን የሚወክሉ ሰዎች ስብስብ/ቡድን" ወይም "በርካታ መልዕክተኞች"

እንዲህም ሆነ

እዚህ ስፍራ ይህ ሀረግ የዋለው በታሪኩ ውስጥ አስፈላጊ ትዕይንተን ለማመልከት ነው፡፡ የእናንተ ቋንቋ ይህንን ለማድረግ መንገድ ካለው፣ እዚህ ላይ ያንን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

መንግሥቱን ከተቀበለ በኋላ

"ከነገሠ በኋላ"

ወደ እርሱ አስጠራቸው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ወደ እርሱ እንዲመጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ምን ያህል እንዳተረፉ

"ምን ያህል ገንዘብ እንዳስገኙ"