am_tn/luk/19/11.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ለተሰበሰበው ሕዝብ በግብረገባዊ ምሳሌ ማስተማር ጀመረ፡፡ ቁጥር 11 ኢየሱስ ለምን ግብረገባዊ ምሳሌውን እንደሚናገር የመረጃ ዳራ ይሰጣል፡፡ (ግብረገባዊ ምሳሌ እና የመረጃ ዳራ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር መንግሥት በቶሎ የሚገለጥ

አይሁዶች መሲሁ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጣ በቶሎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይመሰርታል ብለው ያምኑ ነበር፡፡ "ኢየሱስ በቶሎ በእግዚአብሔር መንግስት ላይ መግዛት ይጀምራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ መስፍን

"ከገዢው መደብ አባል የሆነ አንድ ሰው" ወይም "ከከፍተኛ ቤተሰብ የሆነ አንድ ሰው"

ለራሱ የንጉሥነትን ማዕረግ ለመቀበል

ይህ ታናሽ ንግሥና ያለው ታላቅ ንግሥና ወዳለው መሄዱን ያሳያል፡፡ ታላቁ ንጉሥ ለታናሹ ንጉሥ በራሱ መንግሥት ላይ እንዲገዛ መብት እና ሥልጣን ይሰጠዋል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)