am_tn/luk/19/08.md

1.5 KiB

ጌታ

"ይህ ኢየሱስን ያመለክታል"

አራት እጥፍ አድርጌ

"ከእነርሱ የወሰደኩትን አራት እጠፍ አድርጌ እመልሳለሁ"

ለዚህ ቤት መዳን ሆነ

መዳን ከእግዚአብሔር እንደሚመጣ ይታወቃል፡፡ "እግዚአብሔር ይህንን ቤት አዳነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ይህ ቤት

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው ቃል የሚያመለክተው በቤቱ ወይም በቤተሰቡ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱም ደግሞ

"ይህም ሰው ደግሞ" ወይም "ዘኬዎስም ጭምር"

የአብርሃም ልጅ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "የአብርሃም ትውልዶች/ዘር" እና 2) "እንደ አብርሃም እምነት ያለው ሰው፡፡"

የሰው ልጅ የመጣው

ኢየሱስ ስለ ራሱ እየተናገረ ነው፡፡ "እኔ፣ የሰው ልጅ፣ የመጣሁት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የጠፉትን ሰዎች

"ከእግዚአብሔር የራቁትን ሰዎች" ወይም "በኃጢአታቸው ከእግዚአብሔር የራቁትን"