am_tn/luk/18/38.md

987 B

ስለዚህ

ይህ ቃል አስቀድሞ በሆነ አንድ ሌላ ነገር ምክንየት የሆነን ትዕይንት ያመለክታል፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ የተሰበሰበው ሕዝብ ለዐይነ ስውሩ ኢየሱስ እያለፈ እንደሆነ ነግረውታል፡፡

ከፍ ባለ ድምጽ ጮኸ

"ተጣራ" ወይም "ጮኸ"

የዳዊት ልጅ

ኢየሱስ የእሥራኤል ታላቅ ንጉስ፣ የዳዊት ትውልድ ነበር

ማረኝ

"ራራልኝ" ወይም "ርህራሄህን አሳየኝ"

ከፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩት

"ከተሰበሰበው ሕዝብ ከፊት ይሄዱ የነበሩ ሰዎች"

ዝም እንዲል

"ጸጥ እንዲል" ወይም "እንዳይጮህ"

ይልቁንም አብዝቶ ጮኸ

ይህ ማለት ይበልጥ ድምጹን ከፍ አድርጎ ጮኸ ማለት ሊሆን ይችላል ወይም ይበልጥ ሳያቋርጥ በጽናት ጮኸ ማለት ይሆናል፡፡