am_tn/luk/18/35.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ሲቃረብ ዐይነስውሩን ሰው ፈወሰ፡፡ ይህ ቁጥር የመረጃ ዳራ እና ታሪኩ መቼ እና የት ስፍራ እንደተፈጸመ መረጃ ይሰጣል፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህም ሆነ

እዚህ ስፍራ ይህ ሀረግ የዋለው የታሪኩን አዲስ ክፍል ጅማሬ ለማመልከት ነው፡፡ (አዲስ ትዕይንት ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ዐይነስውር ሰው ተቀምጦ ነበር

"አንድ ዐይነስውር ተቀምጦ ነበር፡፡" እዚህ ስፍራ "አንድ" የሚለው ይህ ሰው ለታሪኩ ጠቃሚ ሆኖ መተዋወቁን ሲያመለክት ሉቃስ በስም አልጠቀሰውም፡፡ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ተሳታፊ ነው፡፡ (አዲስ እና ነበር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

መለመን፣ እና መስማት

እዚህ ስፍራ አዲስ ዐረፍተ ነገር መጀመር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ "መለመን፡፡ በሰማ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እነርሱ ነገሩት

"በሕዝብ ጭንቅንቅ ውስጥ የሚገኙት ሰዎች ለዐይነ ስውሩ ነገሩት"

የናዝሬቱ ኢየሱስ

ኢየሱስ የመጣው በገሊላ ከምትገኘው፣ ከናዝሬት ከተማ ነው

እያለፈ ነበር

"እርሱን እያለፈ እየሄደ ነበር"