am_tn/luk/18/34.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ቁጥር የዋናው ታሪክ ክፍል አይደለም፣ ነገር ግን ስለዚህ ታሪክ ከፍል አስተያየት ነው፡፡ (የታሪክ መጨረሻ/ማጠቃለያ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ ምንም አልተረዱም

"እነርሱ ከእነዚህ ነገሮች መሃል አንዳች አልገባቸውም"

እነዚህ ነገሮች

ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም እንዴት እንደሚሰቃይ እና እንደሚሞት የሰጠውን ገለጻ፣ እና እርሱ ከሞት እንደሚነሳ ነው፡፡

ይህ ቃል ከእነርሱ ተሰውሮ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ ነገር ግን ቃሉን ከእነርሱ የሰወረው እግዚአብሔር ይሁን ወይም ኢየሱስ ግልጽ አይደለም፡፡ "ኢየሱስ መልእክቱን ከእነርሱ ሰወረው" ወይም "እግዚአብሔር ኢየሱስ ለእነርሱ ይነግራቸው የነበረውን መልዕክት ትርጉም እንዳይረዱት ከለከላቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የተባሉ/የተነገሩ ነገሮች

x