am_tn/luk/18/31.md

2.6 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ይህ በዚህ የታሪክ ክፍል በሉቃስ 17፡20 የጀመረው ቀጣይ ትዕይንት ነው፡፡ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ብቻ እየተናገረ ነው፡፡

አሥራ ሁለቱን ወደ ራሱ ሰበሰበ

ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ከሌሎች ሰዎች ፈቀቅ አድርጎ ወስዶ

እነሆ

ይህ በኢየሱስ አገልግሎት ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ጉልህ ለውጥ ያመለክታል

በነቢያት ተጽፎ የነበረ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ነቢያት ጽፈውት የነበረ/ነቢያት የጻፉት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቢያቱ

ይህ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ያመለክታል፡፡

የሰው ልጅ…እርሱ…የእርሱ…የእርሱ …እርሱ

ኢየሱስ ስለ ራሱ "የሰው ልጅ" በማለት ይናገራል፡፡ " እኔ፣ የሰው ልጅ፣… እኔ…ራሴ…ራሴ…እኔ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ይፈጸማል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ይሆናል" ወይም "ይከሰታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ለአሕዛብ ተላልፎ ይሰጣል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የአይሁድ መሪዎች ለአህዛብ አሳልፈው ይሰጡታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ያፌዙበታል፣ እናም በሀፍረት ያንገላቱታል፣ ደግሞም ይተፉበታል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ያፌዙበታል፣ በሀፍረት ያንገላቱታል፣ ደግሞም ይተፉበታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በሦስተኛው ቀን

ይህ ከሞቱ በኋላ ሶስተኛውን ቀን ያመለክታል፡፡ ሆኖም፣ ደቀ መዛሙርቱ ይህንን አልተረዱም፣ ስለዚህም ይህንን ገለጻ ይህ ቁጥር ሲተረጎም አለመጨመሩ ይመረጣል፡፡ (ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)