am_tn/luk/18/18.md

2.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ይህ በሉቃስ 17፡20 ላይ የጀመረው ታሪክ ተከታይ ትዕይንት ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ስለ መግባት ከአንድ የሃይማኖት መሪ ጋር መነጋገር ጀመረ፡፡

አንድ መሪ

ይህ በታሪኩ ውስጥ አንድ አዲስ ገጸባህሪ ያስተዋውቃል፡፡ ይህ ሰው በስልጣኑ ብቻ እንዲታውቅ/እንዲለይ ሆኗል፡፡ (አዲስ እና ነበር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ምን ማድረግ ይገባኛል

"ምን ማድረግ ይኖርብኛል" ወይም "ከእኔ ምን ይጠበቃል"

የዘለዓለም ሕይወት መውረስ

"መጨረሻ የሌለው ሕይወት መቀበል፡፡" "መውረስ" የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው አንድ ሰው ሲሞት ለልጆቹ የሚተውላቸውን ሃብት ነው፡፡ ስለዚህ፣ ይህ ዘይቤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተረድቷል እናም እግዚአብሔር የዘለዓለም ሕይወት እንዲሰጠው ይፈልጋል ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስለምን መልካም ትሉኛላችሁ? ከእግዚአብሔር በቀር ማንም መልካም የለም

ኢየሱስ ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው የሃይማኖት መሪው ለጠየቀው ጥያቄ በቁጥር 18 ላይ እርሱ የሰጠውን መልስ መሪው እንደማይወደው ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኢየሱስ መሪው የእርሱን ጥያቄ እንዲመልስለት አይጠብቅም፡፡ ኢየሱስ የሚፈልገው እርሱ ለመሪው ጥያቄ የሰጠው ምላሽ የመጣው፣ ብቻውን መልካም ከሆነው ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሆነ እንዲረዳ ነው፡፡ "ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም መልካም እንዳልሆነ አንተ ታውቃለህ፣ ስለዚህ እኔን መልካም ማለት እኔን ከእግዚአብሔር ጋር መነጻጸር ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አትግደል

"የሰው ነፍስ አታጥፋ"

እነዚህን ነገሮች ሁሉ

"እነዚህን ትዕዛዛት ሁሉ"