am_tn/luk/18/15.md

1.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ይህ በሉቃስ 17፡20 ላይ የጀመረው ታሪክ ተከታይ ትዕይንት ነው፡፡ ኢየሱስ ልጆችን ተቀብሎ ስለ እነርሱ ተናገረ፡፡

ዳሰሳቸው፣ ነገር ግን

ይህ የተለየ ዐረፍተ ነገር ሆኖ ሊተረጎም ይችላል፡ "ዳሰሳቸው፡፡ ነገር ግን"

እነርሱ ገሰጽዋቸው

"ደቀ መዛሙርቱ የልጆቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ኢየሱስ እንዳያመጧቸው ለማስቆም ሞከሩ"

ኢየሱስ ወደ እርሱ ጠራቸው

"ኢየሱስ ሰዎቹ ህጻናቶቻቸውን ወደ እርሱ እንዲያመጡ ተናገረ"

ትንንሽ ልጆች ወደ እኔ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፣ እናም እነርሱን አትከልክሏቸው

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ በአንድነት የተጣመሩት ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች በተለየ መንገድ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "እናንተ በእርግጥ ልጆች ወደ እኔ እንዲመጡ መፍቀድ አለባችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)