am_tn/luk/18/13.md

1.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ምሳሌውን መናገሩን ጨረሰ፡፡ በቁጥር 14፣ ምሳሌው የሚያስተምረውን ነገር ያብራራል፡፡

በሩቅ ቆሞ

"ከፈሪሳዊው ሩቅ ቆሞ፡፡" ይህ ዝቅ የማለት ምልክት ነው፡፡ ራሱን ከፈሪሳዊው አጠገብ መቆም እንደሚገባው ሰው አልቆጠረም፡፡

ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አንስቶ

"ዐይኖቹን ማንሳት" ማለት ወደ አንድ ነገር መመልክት ማለት ነው፡፡ "ወደ ሰማይ ተመለከተ" ወይም "ወደ ላይ ተመለከተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ደረቱን እየደቃ/እየመታ

ይህ የከፍተኛ ሀዘን አካላዊ መግለጫ ምልክት ነው፣ ደግሞም የዚህን ሰው ንስሃ መግባት እና ራሱን ዝቅ ማድረጉን ያሳያል "ሀዘኑን ለማሳየት ደረቱን መታ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔን ኃጢአተኛውን ይቅር በለኝ

"እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ እኔን ማረኝ፡፡ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" ወይም "እግዚአብሔር ሆይ፣ ብዙ ኃጢአት ብፈጽምም እባክህ ይቅር በለኝ"

ይህ ሰው ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ

ጻድቅ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ኃጢአቱን ይቅር ስላለው ነው፡፡ "እግዚአብሔር ቀረጥ ሰብሳቢውን ማረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)