am_tn/luk/18/11.md

1.3 KiB

ፈሪሳዊው ቆሞ እነዚህን ነገሮች ስለ ራሱ ጸለየ

የዚህ ሀረግ የግሪኩ ጽሁፍ ትርጉም ግልጽ አይደለም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ፈሪሳዊው ቆሞ ስለ ራሱ በዚህ መንገድ ጸለየ" ወይም 2) "ፈሪሳዊው ቆሞ በግሉ እንዲህ ጸለየ፡፡"

ዘራፊዎች

ዘራፊዎች ሰዎችን በማስገደድ ወይም የጠየቁትን የማይሰጧቸው ከሆነ እንደሚጎዷቸው ሌሎችን በማስፈራራት የሚሰርቁ ሰዎች ናቸው፡፡

ወይም እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ እንኳን

ፈሪሳዊው ቀረጥ ሰብሳቢዎች እንደዘራፊዎች ኃጢአተኞች፣ በደለኞች እና ዘማውያን ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "እናም እኔ በእርግጥ እንደዚህ ሰዎችን እንደሚያታልል ኃጢአተኛ ቀረጥ ሰብሳቢ አይደለሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ካገኘሁት ሁሉ

"ካገኘሁት ነገር"