am_tn/luk/17/34.md

2.7 KiB

እኔ ግን እላችኋለሁ

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ መናገሩን ሲቀጥል፣ የሚነግራቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ትኩረት ይሰጥ ነበር፡፡

በዚያች ምሽት

ይህ የሚያመለክተው፣ እርሱ፣ የሰው ልጅ በምሽት ቢመጣ ምን እንደሚሆን ነው፡፡

በአንድ አልጋ ላይ ሁለት ሰዎች ይኖራሉ

ትኩረቱ እነዚህ ሁለት ሰዎች ላይ አይደለም፣ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ይወሰዳሉ ሌሎች ይተዋሉ በሚለው ላይ ነው፡፡

አልጋ

"መከዳ" ወይም "ጎጆ"

አንዱ ይወሰዳል፣ ሌላኛው ይቀራል

"አንዱ ሰው ይወሰዳል ሌላው ሰው ይቀራል፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር አንዱን ሰው ይወስደዋል ሌላውን ይተዋል" ወይም "መላዕክት አንዱን ይወስዳሉ ሌላውን ይተዋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንድነት የሚፈጩ ሁለት ሴቶች ይኖራሉ

ትኩረቱ በእነዚህ ሁለት ሴቶች ወይም በክንዋኔያቸው ላይ አይደለም፣ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች መወሰዳቸው ሌሎች መተዋቸው/ሳይወሰዱ መቅረታቸው ላይ ነው፡፡

አብረው ይፈጫሉ

"እህል አብሮ መፍጨት"

አጠቃላይ መረጃ፡

ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ስለ ትምህርቱ ጠየቁት እርሱም መለሰላቸው፡፡

ጌታ ሆይ፣ የት ይሆናል?

"ጌታ ሆይ፣ ይህ የት ይሆናል?"

አካል/በድን ባለበት፣ በዚያ ጥንብ አንሳ ይሰበሰባል

የዚህ አባባል ትርጉም፣ "ይህ ግልጽ ይሆናል" ወይም "ይህን ነገር በሚሆንበት ጊዜ ታውቁታለችሁ፡፡" "የጥንብ አንሳዎች መሰብሰብ በድን መኖሩን እንደሚያሳይ፣ እንደዚሁ ሁሉ እነዚህ ነገሮች የሰው ልጅ መምጫ መሆኑን ያሳያሉ" (ምሳሌያዊ አነጋገሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ጥንብ አንሳዎች

ጥንብ አንሳዎች በአንድነት የሚበሩ እና ያገኙትን በድን ስጋ የሚመገቡ ትላልቅ ወፎች ናቸው፡፡ እነዚህን ወፎች በዚህ መንገድ መግለጽ ትችላላችሁ ወይም ይህንን የሚያደርጉ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ወፎችን ስም መጠቀም መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ (የማይታወቁትን መተረጎም የሚለውን ይመልከቱ)