am_tn/luk/17/25.md

2.4 KiB

ነገር ግን በመጀመሪያ እርሱ መከራ መቀበል ይኖርበታል

"ነገር ግን በመጀመሪያ የሰው ልጅ መከራ መቀብል ይኖርበታል፡፡" ኢየሱስ ስለ ራሱ በሶስተኛ መደብ እየተናገረ ነው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚሉትን ይመልከቱ)

በትውልዱ መናቅ/መወገድ ይኖርበታል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር መገለጽ ይኖርበታል፡፡ "የዚህ ትውልድ ሰዎች እርሱን መቃወም/ ማስወገድ ይኖርባቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ በሚሆንበት ጊዜ…እንዲህ ቢሆንም እንኳን

"ሰዎች ነገሮችን በማከናወን ላይ ሳሉ…ሰዎች ተመሳሳይ ነገሮችን እያደረጉ ሳሉ"

በኖህ ዘመን

"የኖህ ዘመን" ይህ እግዚአብሔር የዓለምን ሕዝብ ከመቅጣቱ አስቀድሞ ኖህ በኖረበት ዘመን ያለውን ወቅት ያመለክታል፡፡ "ኖህ ይኖር በነበረበት ዘመን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በሰው ልጅ ቀናት

"የሰው ልጅ ቀናት" የሚለው የሚያመለክተው ልክ የሰው ልጅ ከመምጣቱ አስቀድሞ ያለውን ወቅት ነው፡፡ "የሰው ልጅ ሊመጣ ባለበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው"

ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይጋባሉ፣ ደግሞም ልጆቻቸውን ይድራሉ

ሰዎች መደበኛ ነገሮችን ያደርጋሉ፡፡ እግዚአብሔር ሊፈርድባቸው እንደሆነ አያውቁም ወይም ለዚህ ግድ አይላቸውም፡፡

ልጆቻቸውን ይድራሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን እንዲያገቡ ለወንዶች ይፈቅዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

መርከቡ/የኖህ መርከብ

"ታንኳ" ወይም "ጀልባ"

ሁሉንም አጠፋቸው

ይህ ኖህን እና በመርከቧ ውስጥ የነበሩ ቤተሰቦቹን አያጠቃልልም፡፡ "በጀልባዋ ውስጥ ያልገቡትን ሁሉ አጠፋ"