am_tn/luk/17/20.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ የት እንደሆነ እንኳን አናውቅም፤ ይህ የሆነው አንድ ቀን ኢየሱስ ከፈሪሳውያን ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ ነው፡፡

የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ እንደሚመጣ ፈሪሳውያን በጠየቁት ጊዜ፣

ይህ የአዲሱ ትዕይንት መጀመሪያ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች "አንድ ቀን" ወይም "አንድ ወቅት" በማለት ይጀምራሉ፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንድ ዕለት ፈሪሳውያን ኢየሱስን እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፣ ‘የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?'" (አዲስ ትዕይንትን ማስተዋወቅ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ እንደዚሁም ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅሶች የሚሉትን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር መንግስት በውስጣችሁ/በመካከላችሁ ናት

"መንግሥት" የሚለው ስም ጽንሰ ሀሳብ "መግዛት" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር በውስጣችሁ ይገዛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይምለከቱ)

የእግዚአብሔር መንግሥት በእናንተ ውስጥ ናት

ኢየሱስ እርሱን ከሚጠሉ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ይነጋገር ነበር፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "እናንተ" የሚለው ቃል ሰዎችን በአጠቃላይ ያመለክታል፡፡ "የእግዚአብሔር መንግሥት በሰዎች ውስጥ ናት" ወይም 2) "በውስጣችሁ" የሚለው ቃል የተተረጎመው "በመሃላችሁ" በሚል ነው፡፡ "የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡