am_tn/luk/17/17.md

2.6 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ይህ ኢየሱስ አስሩን ለምጻሞች ስለ ፈወሰበት ታሪክ የመጨረሻው ክፈል ነው፡፡

ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ

ኢየሱስ አንዱ ሰው ስላደረገው ምላሽ ሰጠ፣ የተናገረው ግን በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች ነበር፡፡ "ስለዚህም ኢየሱስ ለተሰበሰበው ሕዝብ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አስሩ አልነጹም ነበርን?

ይህ ከሶስቱ ቃለምልልሳዊ ጥያቄዎች የመጀመሪያው ነው፡፡ ኢየሱስ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመባቸው ከተፈወሱት መሃል እግዚአብሔርን ለማክበር የመጣው አንዱ ብቻ በመሆኑ ምን ያህል እንደተደነቀ እና እንዳዘነ በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች ለማሳየትነው፡፡ "አስር ሰዎች ተፈውሰው ነበር፡፡" ወይም "እግዚአብሔር አስር ሰዎችን ፈወሰ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህ ባዕድ በስተቀር፣ ለእግዚአብሔር ክብር ለመስጠት የተመለሱ የሉምን?

ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከዚህ ባዕድ በስተቀር ለእግዚአብሔር ክብር ለመስጠት ማንም ተመልሶ አልመጣም!" ወይም "እግዚአብሔር አስር ሰዎች ፈወሰ፣ ሆኖም ይህ ባዕድ ብቻ ለእግዚአብሔር ክብር ለመስጠት ተመልሶ መጣ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ባዕድ

ሳምራውያን አይሁድ ያለሆነ ዝርያ አላቸው፤ እናም እነርሱ እግዚአብሔርን አይሁዶች በሚያመልኩበት ተመሳሳይ መንገድ አያመልኩም፡፡

እምነትህ አድኖሃል/ደህና አድርጎሃል

"በእምነትህ ምክንያት ድነሃል/እምነትህ አድኖሃል፡፡" "እምነት" የሚለው ሀሳብ "እምነት" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በማመንህ ምክንያት፣ ዳግም ደህና ሆነሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)