am_tn/luk/17/05.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር በሚናገሩበት ወቅት የተፈጠረ አጭር ጊዜ በኢየሱስ ትምህርተ መሃል አለ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ማስተማሩን ቀጠለ፡፡

እምነታችንን አሳድግ/ጨምርልን

"እባክህ የበለጠ እምነት ስጠን" ወይም "በእምነታችን ላይ ተጨማሪ እምነት ስጠን"

የሰናፍጭ ፍሬ የሚያክል እምነት ቢኖራችሁ

የሰናፍጭ ፍሬ በጣም ትንሽ ፍሬ ነው፡፡ ኢየሱስ ትንሽ እምነት እንኳን እንደሌላቸው እያመለከተ ነው፡፡ "የሰናፍጭ ፍሬ የሚያክል ትንሽ እምነት እንኳን ቢኖራችሁ፣ እናንተ" ወይም "እምነታችሁ የሰናፍጭ ፍሬ ያህል አይደለም- ነገር ግን ቢሆን ኖሮ፣ እናንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእንጆሪ ዛፍ

የዚህ አይነት ዛፍ የሚታወቅ ካልሆነ፣ ሌላ አይነት ዛፍ መተካት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ "የሾላ ዛፍ" ወይም "ዛፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የማይታወቀውን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ተነቅሎ፣ በባህር ይተከል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ራሳችሁ ነቅላችሁ ራሳችሁ በባህር ትከሉት" ወይም "ከመሬት ነቅላችሁ በውቅያኖስ ወለል ትከሉት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ይሆንላችኋል/ይታዘዛችኋል

"ዛፉ ይታዘዛችኋል፡፡" ይህ ውጤት ቅድመ ሁኔታዊ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው እምነት ካላቸው ብቻ ነው፡፡