am_tn/luk/17/03.md

1.2 KiB

ወንድምህ ቢበድል

ይህ ምናልባት ወደፊት ሊሆን ስለሚችል ድርጊት የሚናገር ሁኔታዊ ዐረፍተ ነገር ነው፡፡

ወንድምህ

እዚህ ስፍራ "ወንድም" የሚለው ቃል የዋለው ተመሳሳይ እምነት ያለው ሰው በሚለው ስሜት ነው፡፡ "መሰል አማኝ"

እርሱን ገስጸው

"የሰራው ስህተት እንደሆነ በብርቱ ንገረው" ወይም "እርሱን አርመው"

ሰባት ጊዜ ቢበድልህ

ይህ መላምታዊ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ፈጽሞ ላያጋጥም ይችላል፣ ነገር ግን ቢያጋጥም እንኳን ኢየሱስ ሰዎች ይቅር እንዲሉ ይናገራል፡፡(መላምታዊ ሁኔታ የሚለውን ይመልከቱ)

በቀን ውስጥ ሰባት ጊዜ፣ ደግሞም ሰባት ጊዜ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስት ሰባት ቁጥር ለሙሉነት ምሳሌ/ምልክት ነው፡፡ "በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ፣ ደግሞም በእያንዳንዱ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)