am_tn/luk/16/14.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

በቁጥር 14 ላይ ፈሪሳውያን በኢየሱስ ላይ እንዳፉዙበት የመረጃ ዳራ እንደሚጥ ይህ በኢየሱስ ትምህርት ማቆሚያ/ማረፊያ ነው፡፡ በቁጥር 15 ኢየሱስ ትምህርቱን ይቀጣላል ደግሞም ለፈሪሳውያን ምላሽ ይሰጣል፡፤ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)

አሁን

ይህ ቃል ወደ መረጃ ዳራው ያመለክታል

ገንዘብ ወዳጅ የነበሩት

"ገንዘብ እንዲኖራቸው የሚወዱ" ወይም "ለገንዘብ በጣም ስስታም የነበሩ"

አፌዙበት

"ፈሪሳውያን በኢየሱስ ላይ አፌዙ"

እንዲህ አላቸው

"ኢየሱስ ለፈሪሳውያን እንዲህ አላቸው"

በሰዎች ፊት ራሳችሁን ትክክለኛ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ

"ራሳችሁን በሰዎች ፊት መልካም አድርጋችሁ ለማሳየት ትሞክራላችሁ"

እግዚአብሔር ልቦቻችሁን ያውቃል

እዚህ ስፍራ "ልቦች" የሚለው የሚያመለክተው የሰዎችን ፍላጎት ነው፡፡ "እግዚአብሔር እውነተኛ ፍላጎቶቻችሁን ያውቃል" ወይም "እግዚአብሔር ለምን እንደምታደርጉ አንቀሳቃሽ ምክንያታችሁን/ሰበበ ነገራችሁን ያውቃል" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰዎች መሃል ራሱን ከፍ የሚያደርግ በእግዚአብሔር ዐይኖች የተጣላ ነው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎች በጣም ጠቃሚ ናቸው ብለው የሚያስቧቸው ነገሮች እግዚአብሔር የሚጠላቸው ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)