am_tn/luk/16/05.md

1.8 KiB

ከእርሱ አለቃ ተበዳሪዎች/ባለዕዳዎች

"የአለቃው ንብረት ብድር የነበረባቸው ሰዎች" ወይም "የእርሱ አለቃ ሀብት በእጃቸው የነበረ ሰዎች፡፡" በዚህ ታሪክ ውስጥ ተበዳሪዎች/ባለዕዳዎቹ የነበረባቸው የወይራ ዘይት እና ስንዴ ነበር፡፡

እርሱ አለ…እርሱ እንዲህ አለው

"ተበዳሪው/ባለዕዳው አለ… አስተዳዳሪው ለባለዕዳው እንዲህ አለው"

አንድ መቶ ማድጋ የወይራ ዘይት

ይህ ወደ 3,000 ሊትር የወይራ ዘይት ነው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበረ የመጠን መለኪያ)

መቶ…ሀምሳ…ሰማንያ

"100…50…80" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

የውል ወረቀትህን ውሰድ

"የውል ወረቀት" አንድ ሰው ምን ያህል እንዳለበት የሚያሳይ ወረቀት ነው፡፡

አስተዳዳሪው ሌላውንም ሰው… እንዲህ አለው…ለእርሱ እንዲህ አለ

"አስተዳዳሪው ለሌላው ተበዳሪ እንዲህ አለ…ተበዳሪው/ባለዕዳው እንዲህ አለ…አስተዳዳሪው ባለእዳውን አለው

መቶ ዳውላ ስንዴ

ይህን ወደ ዘመናዊ መለኪያ መለወጥ ትችላላችሁ፡፡ "ሃያ ሺህ ኪሎ ስንዴ" ወይም "አንድ ሺህ ቅርጫት ስንዴ" (መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበረ የመጠን መለኪያ)

ሰማንያ ብለህ ጻፍ

"ሰማንያ ዳውላ ስንዴ ብለህ ጻፍ፡፡" ይህን ወደ ዘመናዊ መለኪያ መለወጥ ትችላላችሁ፡፡ "አሥራ ስድስት ሺህ ኪሎ ስንዴ" ወይም "ስምንት መቶ ቅርጫት ብለህ ጻፍ"