am_tn/luk/16/01.md

1.7 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ሌላ ግብረገባዊ ምሳሌ መናገር ጀመረ፡፡ ይህም ስለ አንድ ጌታ እና ገንዘቡን ስለሚያበድርለት አስተዳዳሪ ነበር፡፡ ይህም ቢሆን በሉቃስ 15፡3 ውስጥ የጀምረው ተመሳሳይ ታሪክ ክፍል እና በተመሳሳይ ቀን የተናገረው ነው፡፡ (ግብረገባዊ ምሳሌ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ

ምንም እንኳን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ተሰብስቦ ከሚያደምጠው ሕዝብ ውስጥ ቢሆኑም፣ የመጨረሻው ክፍል ፈሪሳውያንን እና ጸሐፍትን ያመለክታል፡፡

አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር

ይህ በግብረገባዊ ምሳሌው ውስጥ አዲስ ገጸባህሪን ያስተዋውቃል፡፡ (አዲስ እና ነበር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ ተነገረው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎች ለባለጸጋው ሰው ነገሩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሃብቱን እያባከነ እንደሆነ

"የባለጸጋውን ሰው ንብረት በንዝህላልነት እያስተዳደረ እንደሆነ"

ይህ ስለ አንተ የምሰማው ነገር ምንድን ነው?

ባለጸጋው ሰው ጥያቄውን ያነሳው የሃብቱን አስተዳዳሪ ለመገሰጽ ነው፡፡ "እያደረግህ የምትገኘውን ሰምቻለሁ፡፡" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)