am_tn/luk/15/28.md

2.6 KiB

እነዚህ ብዙ አመታት

"ለብዙ አመታት"

ለአንተ ባሪያ ሆንኩ

"ለአንተ እጅግ በከባዱ ሰራሁ" ወይም "ለአንተ እንደ ባሪያ በከባዱ ሰራሁ"

በፍጹም የአንተን አንዲት ህግ አልጣስኩም

"በፍጹም ከትእዛዝህ አልወጣሁም" ወይም "ሁልጊዜም አድርግ ያልከኝን ሁሉ አድርጌያለሁ"

አንዲት ትንሽ ፍየል

ትንሽ ፍየል ከሰባ ጥጃ ያነሰች እና ዋጋዋም ዝቅተኛ ነበረች፡፡ "ትንሽ ፍየል እንኳን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ልጅ

"ያ የአንተ ልጅ፡፡" ትልቁ ልጅ ወንድሙን በዚህ መንገድ የሚገልጸው ምን ያህል እንደተናደደ ለማሳየት ነው፡፡

ሀብትህን/ኑሮህን በላ

ምግብ ለገንዘብ ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ አንድ ሰው ምግብን ከተመገበው በኋላ፣ ምግቡ ዳግመኛ አይበላም፡፡ ወንድሙ ከወሰደው ገንዘብ አንዳች አልተረፈም፤ ምንም ነገር አልቀረም፡፡ "ሀብትህን ሁሉ አባከነ" ወይም "ገንዝብህን ሁሉ በተነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከጋለሞቶች ጋር

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ወንድሙ ገንዘቡን ያባከነው እንደዚህ ነው ብሎ ገምቷል፣ ወይም 2) ስለ ጋለሞቶች የተናገረው "በሄደበት ሩቅ አገር" ወንድሙ የሰራቸውን የኃጢአተኝነት ድርጊቶች ለማጋነን ነው (ሉቃስ 15፡13)፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

የሰባ ጥጃ

ጥጃ ገና በሬ ያለሆነ ነው፡፡ ሰዎች ጥጃዎች በሚገባ እንያድጉ ጥሩ አድረገው ይቀለቀቧቸዋል፤ ከዚያም የተለየ ድግስ ሲኖርባቸው ይመገቧቸዋል/አርደው ይበሏቸዋል፡፡ይህ ሀረግ በሉቃስ 15፡23 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "የሰባው/ምርጡ ጥጃ" "ያሰባነው ወይፈን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)