am_tn/luk/15/22.md

2.3 KiB

ምርጥ ካባ/ልብስ

"በቤት ካለው ምርጡን ልብስ፡፡" "ምርጡን ኮት" ወይም "ምርጡን ጨርቅ"

ለጣቱ ቀለበት አድርጉለት

ቀለበት ወንዶች ከጣታቸው መሃል በአንዱ የሚያጠልቁት የስልጣን ምልክት ነበር፡፡

ነጠላ ጫማ

በዘመኑ ባለጸጋ ሰዎች ነጠላ ጫማ ያደርጉ ነበር፡፡ ሆኖም፣ በብዙ ባህሎች የዚህ ዘመናዊ አቻ የሆነው "ጫማ" ነው፡፡

የሰባ ጥጃ

ጥጃ ገና በሬ ያለሆነ ነው፡፡ ሰዎች ጥጃዎች በሚገባ እንያድጉ ጥሩ አድረገው ይቀለቀቧቸዋል፤ ከዚያም የተለየ ድግስ ሲኖርባቸው ይመገቧቸዋል/አርደው ይበሏቸዋል፡፡ "የሰባውን ፍሪዳ" ወይም "በሚገባ ያባነውን ወይፈን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እረዱ

ለምን ፍሪዳው እንደታረደ በውስጠታዋቂነት ያለው መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "አርዳችሁ ስሩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ልጄ ሞቶ ነበር፣ አሁን በሕይወት አለ

ይህ ዘይቤ የሚናገረው የኮበለለውን ልጅ እንደሞተ አድርጎ ነው፡፡ "ልጄ ከሞተ በኋላ ዳግም ህያው እንደሆነ ይቆጠራል" ወይም "ልጄ ሞቶ እንደነበረ እና አሁን ዳግም ህያው እንደሆነ ይሰማኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጠፍቶ ነበር፣ አሁን ተገኘ

ይህ ዘይቤ የሚናገረው የልጁን መኮብለል/መሄድ እንደጠፋ አድርጎ ነው፡፡ "ልጄ ጠፍቶ ነበር አሁን ግን አገኘሁት" ወይም "ልጄ ጠፍቶ ነበር አሁን ቤት ተመለሰ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)