am_tn/luk/15/20.md

2.2 KiB

ስለዚህም ታናሹ ልጅ ወደ አባቱ ተመለሰ

"ስለዚህ ከሄደበት አገር ወደ አባቱ ተመለሰ፡፡" "ስለዚህ" የሚለው ቃል የሆነውን ድርጊት አስቀድሞ በሆነው ሌላ ነገር ምክንየት እንደሆነ ያመለክታል፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ ወጣቱ ሰው ሲቸግረው ወደ ቤት ለመመለስ ወሰነ፡፡

ገና ከሩቅ ስፍራ ሳለ

"ገና ከቤቱ ሩቅ ስፍራ ሳለ" ወይም "ገና ከአባቱ ቤት ሩቅ ስፍራ ሳለ"

በርህራሄ ቀረበው

"ለእርሱ ርህራሄ ነበረው" ወይም "እጅግ ከልቡ ይወደው ነበር"

አቅፎ ሳመው

አባቱ ይህን ያደረገው እንደሚወደው ለልጁ ለማሳየት እና ልጁ ተመልሶ ቤት በመምጣቱ ስለተደሰተ ነበር፡፡ ሰዎች አባት ወንድ ልጁን ማቀፉ ወይም መሳሙ እንግዳ ነገር ወይም ስህተት ነው ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ በባህላችሁ አባቶች ለወንድ ልጃቸው ያላቸውን ፍቅር የሚገልጹበትን መንገድ ተክታችሁ መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ "እርሱን በፍቅር ተቀበለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በሰማይ ፊት መበደል

የአይሁድ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ "እግዚአብሔር" የሚለውን ቃል "ሰማይ" በሚል ተክተው ይጠቀማሉ፡፡ ይህ በሉቃስ 15፡18 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እግዚአብሔርን በደልኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ ተመሳሳይ የሆነው ሀረግ በሉቃስ 15፡18 ላ እንዴት እንደ ተተረጎም ይመልከቱ፡፡"ልጄ ብለህ ልትጠራኝ አይገባኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)